አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ለ14 የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
1. ዶ/ር ተስፋዬ ከበደ ለገሰ – በቦዲ ኢሜጂንግ
2. ዶ/ር መሳይ ሙሉጌታ ተፈራ – በሶሺዮ ኢኮኒሚክ ዴቨሎፕመንት ጥናት
3. ዶ/ር ዲንቃ አያና አጋ – በቬተርነሪ ፓራሲቶሎጂ
4. ዶ/ር ፉፋ አቡና ኩራ – በቬተርነሪ ፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ወንደሰን ተስፋዬ አብሬ – በሊንጉዊስቲክስ
6. ዶ/ር አማኑኤል ገብሩ ወ/አረጋይ – በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ጥናቶች
7. ዶ/ር ሙራዱ አብዶ ሱሩር – በሕግ
8. ዶ/ር ክሪስቶፍ ቫነደርቤከን – በፐብሊክ ሎዉ
9. ዶ/ር እሸቴ ብርሃን አጣናው – በኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ
10. ዶ/ር ዋሴ ከበደ ታደሰ – በሶሻል ወርክ
11. ዶ/ር ሰይፈ ተፈሪ ደሌ – በሜዲካል ፊዚክስ ዲያግኖስቲክስ ራዲዮሎጂ
12. ዶ/ር ወርቁ መኮንን – በሰዉ ሃብት አስተዳደር
13. ዶ/ር ሺፈራዉ ታዬ – በስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ
14. ዶ/ር ደረጀ ኃይሉ – በዉሃ ሃብት ኢንጂነሪንግ
ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን÷ ይህም ለዩኒቨርሲቲው አካዳሚያዊ ቁመና ወሳኝ ርምጃ መሆኑ ተመላክቷል፡፡