Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሮጀክቶችን መጨረስ የዚህ መንግስት ልዩ መለያ ባህሪ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፕሮጀክቶችን መጨረስ የዚህ መንግስት ልዩ መለያ ባህሪ ነው አሉ።

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራሽን ዘርፉን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ተግዳሮትና ዕድሎችን በመለየት ዘርፉን ወደ አዲስ ከፍታ ለማሸጋገር በፈረንጆቹ ከ2025 እስከ 2050 ድረስ የሚተገበር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ይፋ ማድረጊያ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ መንግሥት ለዚህ የልዕልና ህልም መሳካት ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ጨምሮ ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን እየተገበረ ይገኛል።

ኢኒሼቲቩ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመፍጠር እንደሚያስችል ገልጸው፤ ቁልፍ ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ተግዳሮቶችን ጭምር በጋራ የሚፈታም ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ኢኒሼቲቩ ቅንጅትን የሚያጠናክር፣ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በአፍሪካ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር፣ በአፈጻጸም ላይ የተመሰረተ የምዘና፣ የእውቅና እና የተጠያቂነት አሰራርን በመዘርጋት በዘርፉ ተወዳዳሪነትን የሚያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ኢኒሼቲቭ የኮንስትራክሽን እሳቤያችንን እንደሀገር የሚቀይር ነው ብለዋል።

በተደመረ አቅም፣ በባለሙያዎቻችን እውቀት፣ በተቋሞቻችን ቅንጅት እና በመንግስት የተሟላ ድጋፍ ኢትዮጵያን የአህጉራችን የልህቀትና የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ነው ያሉት።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version