አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የመደመር መርህ ብሔራዊ መግባባትን እና ዘላቂ ልማትን ይገነባል አሉ፡፡
12ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በጋና አክራ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት፤ የብዙዎቹ ሀገራት ፖለቲካ ለረጅም ጊዜ የሚመራው በስልጣን ሽኩቻ፣ የአጭር ጊዜ አጀንዳዎች እና ፉክክር በመሆኑ የሀገርን ጉልበት እያሟጠጠ ነው።
የፖለቲካ ድርጅቶች እንደራሳቸው ፍላጎት ሳይሆን ሁሉንም የሚካትቱ፣ የበለፀጉ እና ሰላም የሰፈነባቸው ሀገሮች መሣሪያ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ የድርጅት ውህደት ሆኖ ብቻ የተወለደ ሳይሆን ለፖለቲካዊ ማሻሻያዎቻችን ጭምር ማዕከል ያደረገ ፓርቲ መሆኑን አብራርተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መርህ ‘መደመር’ በአንድነት፣ በጋራ አስተዋፅኦ እና በጋራ ዓላማ ሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዟችንን ይወክላል ነው ያሉት።
ፓርቲው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችን አባላት በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች በማካተት እንዲሰሩ ማድረጉን አንስተዋል።
መደመር ብሔራዊ መግባባትን ስለሚፈጥር፣ ብሔራዊ መግባባት ደግሞ አንድነትን፣ መረጋጋትንና ዘላቂ ልማትን ይገነባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ሁሉንም በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ገዥም ሆኑ ተፎካካሪ በአንድ ላይ በማሰባሰብ ወደ ቋሚ የውይይት መድረክ፣ የምክክር እና የጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ማቋቋሟን ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!