አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ማሳያ የሆኑት ሉሲ እና ሰላም በቼክ ሪፐብሊክ በሚገኘው ፕራግ ሙዚዬም ለዕይታ ሊቀርቡ ነው።
የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን በፈረንጆቹ የፊታችን ነሐሴ 25 ጀምሮ በመካከለኛው አውሮፓ ይካሄዳል።
በዚህም የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ማሳያ የሆኑት ሉሲና ሰላም በቼክ ሪፐብሊክ በሚገኘው ፕራግ ሙዚዬም ለዕይታ ይቀርባሉ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ሃብቶች የሚያስተዋውቁ የቢዝነስ ፎረሞች፣ የጥበብ ሥራዎች ኤግዚቢሽንና ሌሎች መድረኮች ይካሄዳሉ።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በሉሲና ሰላም ቅሪተ አካላት ሽኝት መርሐ ግብር ላይ እንዳሉት ፥ ኤግዚቢሽኑ አዲሲቷን ኢትዮጵያ የምንገልጽበት ነው ።
የፕራግ ሙዚዬም ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚካኤል ሉቸክ በበኩላቸው ፥ መርሐ ግብሩ የዓለም የሰው ዘር መገኛ የሆነችው የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት የምናሳይበት በመሆኑ ታሪካዊ ሁነት ነው ብለዋል።
በቅድስት አባተ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!