Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጌደብ ወንዝ ድልድይ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደብረ ማርቆስ – ባሕርዳር በሚወስደው መንገድ የሚገኘው የጌደብ ወንዝ ድልድይ  ለተሽከርካሪ ክፍት  ተደርጓል አለ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፡፡

አስተዳደሩ ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው ÷ በጎርፍ ጉዳት ደርሶበት የነበረውን የጌደብ ወንዝ ድልድይ በተገጣጣሚ ብረት የመገንባቱ ሥራ ተጠናቅቋል፡፡

በዚህም ድልድዩ በዛሬው እለት  ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ለተሽከርካሪ ክፍት ተደርጓል፡፡

የጌደብ ወንዝ ድልድይ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ጮቄ ተራራ ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በደረሰበት ጉዳት ከደብረ ማርቆስ – ባሕርዳር የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ድልድዩ በጎርፍ ምክንያት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ግንባታው እስኪጠናቀቅ በትዕግስት ሲጠባበቁ ለቆዩ መንገደኞችና አሽከርካሪዎች ምስጋና ቀርቧል፡፡

Exit mobile version