አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ብልጽግናን ሊያመጣ የሚችል የትምህርት ምዘና ሥርዓት መዘርጋት ይገባል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ የትምህርት ምዘናዎች ኅብረት 41ኛው ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ እንዳሉት፤ ትምህርት የክብር እና የብልጽግና መሰረት ነው።
ሁሉም ህጻናት መማር የሚችሉበት ነገ መፈጠር እንዳለበት ጠቅሰው፤ የትምህርት ጥራት ልዩ ችሮታ ሳይሆን ለሁሉም ተደራሽ መሆን እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የትምህርት ምዘናዎች ኅብረት ዓመታዊ ኮንፍረንስ ዓላማም ጥራትና ተደራሽነት መሆኑን ተናግረዋል።
ምዘና ትምህርት የሚታገዝበት መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የት እንዳለን የምንመለከትበት እና ወደ የት እንደምንሄድ የምንመራበትን ጎዳና አመላካች ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዓድዋ ድል መላውን ዓለም ጭቆናን በመቃወም ለጀግነት እና ለአንድነት መቆምን ማስተማሩን ጠቅሰዋል።
ይህ ዛሬም ህያው የሆነው የዓድዋ የነጻነት መንፈስ በትምህርት ዘርፍ መመሪያችን ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጠንካራ የትምህርት ሪፎርም እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸው፤ እኛ የትኛውም ተማሪ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኝ እየሰራን ነው ብለዋል።
ኮንፍረንሱ የተሞክሮ ልውውጥ የሚደረግበት እንዲሁም ፈጠራ እና ጥናቶችን በመጋራት ሃሳቦች ወደተሻለ የከፍታ ምዕራፍ እንዲሻገሩ የሚደረግበት እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
የትምህርት ምዘናን በተመለከተ ኢትዮጵያ የተከተለችው ጎዳና በዕውቀት የሚመራ ተከታታይ የምዘና ስርዓት መሆኑን ገልጸው፤ ፍትሐዊ እና ፋይዳ ያለው እንዲሆን አቅደን ሰርተናል ብለዋል።
ተማሪዎች የሚሰሩበት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱን በመግለጽ፤ ይህም አህጉራዊ የትምህርት ምዘና ማዕቀፍ ተዘርግቶ ወጥነት ያለው አህጉራዊ አሰራርን ለማስፈን የሚያስችል ድልድይ ይሆናል ነው ያሉት።
ወጥነት ያለው አህጉራዊ አሰራር የተማሪዎች እና የመምህራንን እንቅስቃሴ ቀላል እንዲሆን ያስችላል ሲሉ ነው የገለጹት።
ብዝሐነትን የጠበቀ ንጽጽር እና ውድድር እንዲኖር ያስችላል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገር በቀል እውቀቶችን ለመጠበቅ፤ ልዩ ስርዓተ ትምህርት ለመተግበር እና የኢኮኖሚ ህልሞቻችንን ለማሳካት ያስችለናል ብለዋል።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!