አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቶተንሃም ሆትስፐር ሊቀ መንበር ዳንኤል ሌቪ ከሃላፊነት መልቀቃቸውን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ዳንኤል ሌቪ የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር ለ25 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን÷ ስፐርስ በሌቪ የስልጣን ዘመን ብዙ ለውጦችን አሳይቷል።
የ63 ዓመቱ ዳንኤል ሌቪ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም በነበራቸው ቆይታ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ፓውንድ ለተጫቾች ዝውውር ወጪ አድርገዋል።
የቀድሞ ሊቀመንበር 12 አሰልጣኞችን በቆይታቸው የቀጠሩ ሲሆን ÷ ሁለት ዋንጫዎችንም አሳክተዋል።
ዳንኤል ሌቪ በቶተንሃም ቆይታቸው በሰሩት ሥራ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸው ለክለቡ ደጋፊዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!