Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሁለንተናዊ የተቋም ማዘመን ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለንተናዊ የተቋም ማዘመን ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

‎የተሟላ ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚችለው የቆሬ ሜንተናንስና ዕድሳት ማዕከል ተመርቋል።

በዚህ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የመከላከያ ሰራዊቱን በሁሉም ዘርፍ የማዘመን ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

‎ከ8 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ ላይ የተገነባው የቆሬ ሜንተናንስና ዕድሳት ማዕከል 12 ወርክ ሾፖች፣ የአስተዳደር ህንጻ፣ ነዳጅ ማደያንና አረንጓዴ ስፍራዎችን ያካተተ ነው።

‎ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት የቆየና ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የተለያዩ ማሻሻያዎች ተደርገውለት መከላከያንም ኢትዮጵያንም በሚመጥን ልክ መገንባቱ ተገልጿል።

‎በጃንሜዳና በሜክሲኮ በተበታተነ መልኩ ሲሰጥ የነበረን አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከል ያመጣው የቆሬ ሜንተናንስና ዕድሳት ማዕከል የአገልግሎት ጥራትን ያረጋገጠ መሆኑን ተመላክቷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version