Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ያለውን ጳጉሜን 1 የጽናት ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፤ ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው ብለዋል።

በሁሉም ዘርፎች በምናደርገው ተጋድሎ የኢትዮጵያን መሠረት እናጸናለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለማናቸውም ችግሮች የማትበገር፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የምትቀይር፣ በመጪው ዘመንም ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version