Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ መሶብ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት የማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት የማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በመዲናዋ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮውን ዘመን ስናበቃ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀና ቀልጣፋ መሆኑን ለማረጋገጥ የነበረን ቁርጠኝነት እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፌደራል አገልግሎቶች ወደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በአዲሱ አመት ዋዜማ በ13ተቋማት 107 የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመልክተናል ነው ያሉት።

ይህም አገልግሎት አሰጣጥን የመልካም አስተዳደር የድንጋይ ማዕዘን የማድረግና ለዜጎች ወቅቱን የጠበቀ፣ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት የማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

በአዲሱ አመት ገና ብዙ ማዕከላት ይኖሩናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በድጋሚ ለአዲሱ አመት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version