አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአዲሱ ዓመት ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ሰላምን የማጽናት ስራዎቹን አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የ2018 አዲስ ዓመትን አስመልክተው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ በሀገር ውስጥማ በውጭ በግዳጅ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ‘እንኳን አደረሳችሁ’ ብለዋል።
2017 ዓ.ም ሠራዊቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በድል የተወጣበት ዓመት በመሆኑ የተሻለ የሰላም ድባብ የታየበት ዓመት ሆኖ አልፏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ሠራዊቱ የሀገር ሉዓላዊነት የመጨረሻ ምሽግ መሆኑን በተግባር አሳይቷል ነው ያሉት፡፡
ለዚህም ከፍተኛ ክብርና ምስጋና አለኝ ብለዋል።
2018 ዓ.ም የተጀመሩ ስራዎች የሚጠናቀቁበት እና ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ ተፈትተው ሀገራችን ወደ ተሟላ ሰላም የምትሸጋገርበት ዘመን ይሆናል ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!