አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያስገነባው አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ አኅጉራዊ ትስስርን የማጎልበት እና ምጣኔ ሀብታዊ እድገትን የማፋጠን አቅም ያለው ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው አሉ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ።
አቶ አህመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ለማስገንባት ያቀደውን ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ፕሮጀክት ማሳያ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ነው ይህንን ያሉት፤
አዲሱ የአየር መንገዱ ፕሮጀክት ከሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ እና ፕሮጀክቱ ከትራንስፖርት መዳረሻ ግንባታ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ የአየር መንገዱን አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸው÷ ይህም ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ የዓለም የአቪየሺን መዳረሻዎች እንድትሰለፍ ያስችላታል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ከጥቅል ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያው እና ከዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ግቦች ጋር የተናበበ መሆኑን ጠቅሰው÷ የአካባቢ ሥነ-ምህዳርን ታሳቢ ያደረገ፣ የበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳና አረንጓዴ ከባቢን ለመፍጠር ከተያዙ ግቦች ጋር የሚጣጣም እንደሆነ ተናግረዋል።
በፕሮጀክቱ ግንባታ ዓለም አቀፋዊ ስታንዳርዶችን የተከተለ እንዲሆን እየተሰራ እንደሆነ እና የረጅም ዘመናት ግቦቹ አካባቢያዊና ማህበራዊ ስነምህዳር መሥተጋብርን መሠረት ያደረገ ነው መሆኑን አብራርተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሀገሪቱ የራሷ አቅም በቅርቡ መመረቁ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ሰርቶ ለማጠናቀቅም የኢትዮጵያን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉም አቶ አሕመድ ሺዴ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በስኬት እንዲጠናቀቅ እንደሚያስችል እና የፕሮጀክቱ ስኬት የኢትዮጵያ ቀዳሚ ግብ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ስኬት እንደሚሆን ጠቁመዋል።
በመሳፍንት ብርሌ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!