አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ድህነትን መፀየፍ ብቻ ሳይሆን ብልጽግናን ይመኛል አሉ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ በትናንትናው ዕለት ተመርቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመደመር መንግሥት የኋልዮሽ ተጉዞ ከዳሰሰ በኋላ መዳረሻውን ደግሞ ይተልማል ብለዋል፡፡
የመደመር መንግሥት የኋልዮሽ በመጓዝ ስብራቱ የት ገጠመን፤ የት ነው የተቀደምነው ብሎ የታለፍንበትን ዘመናት ወደ ኋላ በመሄድ ገምግሟል ነው ያሉት፡፡
በዚህ የኋልዮሽ ጉዞ መነሻ ውስጥ የመደመር መንግሥት የተገነዘባቸው አንኳር ዕሳቤዎች እንዳሉም አብራርተዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል አንደኛው የተዛቡ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በትክክል አለመጠየቅ ትክክለኛ ምላሽ እንዳናገኝ ያደርገናል ብለዋል፡፡
ሌላኛው ደግሞ ለተዛባው ጥያቄ አፍራሽ የለውጥ ሂደት መከተል መሆኑን በማንሳት የእኛ ብቃት የሚለካው ትናንትናን በማፍረስ እንጂ የጎደለውን ሞልተን አሸጋግረን በመስጠት አልነበረም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ወዳጆች ጭምር ኩራት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት፣ ረቂቅ፣ ግዙፍ እና በርካታ ሕዝብ ያላት ሀገር መሆኗን ዓለም ያምናል ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ አኩሪ ታሪክና የነጻነት ገድል ያለው፣ በተፈጥሮ የታደለ፣ በባህል እና በታሪክ ምንም የሚያሳፍር ነገር የሌለው ሕዝብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጀግኖች፣ ደፋሮች እና ለሕይወታቸው የማይሳሱ በረዥም ጊዜ ውስጥ ቢለካ ጀግንነታቸው ያልነጠፈ ሕዝቦች መኖሪያ መሆናንም አመልክተዋል፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!