አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አማካሪ የሆኑትን ማሳድ ቡሎስን በጽሕፈት ቤታችን አግኝቼ ሰፊ አድማስ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያየወተናል ብለዋል።