Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀም ግንዛቤ የሚፈጥር እና ሀገራዊ ዘመቻውን የሚያበረታታ ውድድር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀም ግንዛቤ የሚፈጥር እና ሀገራዊ ዘመቻውን የሚያበረታታ ውድድር ይፋ አደረገ።

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ጠቀሜታን የሚያስተዋዉቅ “መስክ ኢትዮጽያ” ዘመቻ በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሰህለወርቅ ዘውዴ ይፋ ተደርጎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

የጤና ሚኒስቴርም ይህ ዘመቻ ከታለመለት ግብ ለማደረስ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀም ግንዛቤ የሚፈጥር እና ሀገራዊ ዘመቻውን የሚያበረታታ ውድድር ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የሚመለከታቸው አካላት የማስክ አጠቃቀም የሚያስተምር፣ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በሚመለከት ግንዛቤን የሚፈጥር እና ሀገራዊ ዘመቻውን የሚያበረታታ የ30 ሰከንድ የቪዲዮ እንዲሁም ፎቶግራፍ እና በሬዲዮ ሊቀርብ የሚችሉ ስራዎችን አወዳድሮ ሊሸልም መዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው moh@moh.gov.et እና www.mascethiopia@gmail.com ኢሜይል እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር ድህረገጽ ላይ በመግባት በተዘጋጀው ሙሉ መረጃ መሰረት እስከ ነሐሴ 18/2012 ዓ/ም ድረስ በመላክ ውድድሩን እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version