አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአሁኑ ትውልድ በላብ፣ በደም እና በሃሳብ ታግሎ ያሸነፈው አንጸባራቂ ድል ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የቀደመ የስልጣኔ ቀለምና ዐሻራ ዛሬ ድረስ ያደመቃት ሐረር የዚህ ትውልድ አሻራ በሆነው ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የልማት ድል ሰልፍ አድርጋለች ብለዋል።
ሕዳሴ በትውልዶች ሁሉ በታላቅ የቃል ግርማ የሚነገር፤ የአሁኑ ትውልድ በላብ፣ በደም እና በሃሳብ ታግሎ ያሸነፈው አንጸባራቂ ድል መሆኑን አውስተዋል፡፡
በሕዳሴ ግድብ የታየው የመቻል ምልክት፣ የትብብር ውጤትና የአብሮነት ጉልበት እንደ ሐረር ላሉ በሰላምና ተከባብሮ መኖርን መሰረት ላደረጉ ክልሎች ትልቅ ዕሴትን ይጨምራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሐረር የዚህ የልማት ድል ነጋሪ ብቻ ሳይሆን ተጋሪ መሆኗን በጀመረቻቸው ልማቶች እያሳየች ትገኛለች ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!