Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለአቅመ ደካሞች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በወንዶገነት ከተማ አስተዳደር ለአቅመ ደካሞች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረክቧል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አድማሱ ዳምጠው ቤቶቹን ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት፤ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከተቋም ተልዕኮ ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
በዚህም በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቁ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እና የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት በወንዶገነት ከተማ ማከናወኑን አስታውሰዋል።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በከተማው ያስገነባቸውን የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች አጠናቅቆ አስረክቧል ብለዋል።
ሀገር የምትገነባው በመደጋገፍ ፣ በመተሳሰብ እና በመተባበር ነው ያሉት አቶ አድማሱ ዳምጠው፤ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆነውን የመደጋገፍ እሴት አጠናክሮ በማስቀጠል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የበጎ ተግባር ሥራ የመረዳዳት፣ መደጋጋፍ እና መተባበር ተምሳሌት መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የወንዶገነት ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሁሴን ከድር ተናግረዋል።
ይህንን የመደጋገፍ እሴት የዘወትር ተግባር ማድረግ እንደሚገባም አመልክተዋል።
በሄብሮን ዋልታው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version