Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት ዙሪያ ከፀጥታ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት ዙሪያ ዛሬ ከፌደራል፣ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በያዝነው ወር የሚከበሩት የመስቀል ደመራ፣ የኢሬቻ እና ሌሎች የሕዝብና የአደባባይ በዓላት በተሳካ ሁኔታ እንዲከበሩና በሰላም እንዲጠናቀቁ የተደረጉ ዝግጅቶችን ገምግመናል ብለዋል።

ከዚህ በፊት የተከናወኑ የበዓል አከባበሮች የፀጥታ አካላት እና ሕዝቡ በጋራ በመሆን በቅንጅት በመስራታቸው ስኬታማና ለመጪዎቹ በዓላት አከባበር ልምድ የተገኘበት መሆኑን ተመልክተናልም ነው ያሉት።

መጪዎቹ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም የፀጥታ ተቋማት በቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘ የተሟላ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በዓላቱ ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተጀምረው በድምቀት እንዲጠናቀቁ የፀጥታ አመራሩና አባላት ከሕብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠናል ሲሉም አመላክተዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version