አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ በርንሌይን ሲያሸንፍ ቼልሲ በብራይተን ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ኢቲሃድ ስታዲየም ላይ በተደረገው ጨዋታ ሲትዝኖቹ በርንሌይን 5 ለ 1 ሲያሸንፍ ÷ ግቦቹን እስቲቭ በራሱ ግብ ላይ (2)፣ ሃላንድ (2) እና ማቲያስ ኑኔዝ አስቆጥረዋል፡፡
በሌላ በኩል ቼልሲ በብራይተን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡
የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ዳኒ ዌልቤክ (2) እና ዲ ሳይፐር ከመረብ አሳርፈዋል፡፡