አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን የበለጠ ከማስፋት በተጓዳኝ የጤና ባለሙያዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አገልጋይና ተገልጋይን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ተደርጓል አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።
ሚኒስትሯ ይህን ያሉት ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የህክምና ባለሙያዎች ሁለት ባለ 16 እና አንድ ባለ 12 ወለል የመኖሪያ ህንጻዎች ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅት ነው።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልና ኮሌጁ በአገልግሎት አሰጣጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን እየተገበሩ ነው ብለዋል።
በሆስፒታሉም ሆነ በኮሌጁ በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና እርካታ የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ጤና ባለሙያዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው÷ ለዚህም መንግሥት አገልጋይና ተገልጋይን ያማከለ የአገልግሎት አሰጣጥ ስትራቴጂን በመተግበር ጥያቄያቸውን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የጤና ባለሙያዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራን ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!