አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእርግጠኝነት ለኢትዮጵያውያን ማረጋገጥ የምፈልገው 3 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዛሬ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን ሪቫን እንቆርጣለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመጀመሪያ ዙር የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ባስመረቁበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ፕሮጀክቱ 1 ሺህ ሜጋ ዋት (በኢነርጂ የማምረት አቅም የሕዳሴን ግማሽ የሚሆን) የጋዝ ኢነርጂ ማምረቻ መሆኑን ገልጸል።
ይህ ሲደጋገም ለኢትዮጵያ ብርሃን ይሆናል፤ በስፋት ኢነርጂ ማምረት መቻል ብዙ ትርጉም እንዳለውና ይህም የጋዝ ፕላንት በምግብ ራሳችንን ለመቻል በምናደርገው ጥረት ለማዳበሪያ ዋነኛ ግብዓት በመሆን እንደሚያገለግል አስረድተዋል።
በዚህ ዓመት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ክልል የሚሄዱ 2 ሺህ የሚጠጉ አውቶብሶችን ወደ ጋዝ እንቀይራለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ እነዚህ መኪናዎች ሲቀየሩ ቢያንስ በሚቀጥለው ዓመት የትራንስፖርት ዋጋ በ50 በመቶ እንደሚቀንስ ተናግረዋል።
ኢነርጂ ስናመርት ጋዝ ምግባችን፣ ትራንስፖርታችን እና ለኢነርጂ ማምረቻ የሚውል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው በማለት በጋዝ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን መጠቀም መቻል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ ሃብት ለሚያወጡ ሀገራት ትርጉሙ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ከባድ ተሽከርካሪዎች አንዴ ጋዝ ከተሞሉ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችሉ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ነዳጅ የሚጠቀም ማንኛውም ከባድ ተሽከርካሪ ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የተከለከለ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ማንኛውም ባለሃብት ጋዝ የሚጠቀሙ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ሲያስገቡ ከቀረጥ ነጻ አገልግሎትን ጨምሮ አስተማማኝ ድጋፍ ይደረጋል ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ወር የጀመረቻቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች ለትንንሽ ችግሮች ትንንሽ መፍትሔ መስጠት ሳይሆን ችግሮችን በመዝለል የመራቅ ስራ ነው ሲሉም አብራርተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!