Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልጽግናን ርዕይ ለማሳካት የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን ያስፈልጋል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግናን ርዕይ ለማሳካት የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና የልማት አቅም ማድረግ ያስፈልጋል አሉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የባሕር ዳር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት።

የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን በፍጥነት እና በፈጠራ የታገዘ የላቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፖሊሲ ተቀርጾ በአዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ ተተርጉሞ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል።

በአዲስ አበባ በሀገር ውስጥ ሃብት እና ክህሎት የተጀመረው ስራ ተሞክሮ ወደ ክልሎችም እየተስፋፋ መሆኑን አንስተዋል።

የባሕር ዳር ከተማም ይህንን ስራ በተግባር ከተቀላቀሉ ከተሞች መካከል ሆናለች ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሕዝቡ ለሚነሱ ተደጋጋሚ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ ዘመናዊ እና በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ስለሆነም ጊዜውን ሰውቶ ከቅርብም ከሩቅም ስራውን አቋርጦ አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣን ሰው በተገቢው መልኩ ማስተናገድ ከፍተኛ የሀገር አገልግሎት ነው ብለዋል።

በቀጣይም የአገልግሎት አሰጣጡን በተመለከተ በተደራጀ መልኩ ለተገልጋዩ መረጃ መስጠት ይገባልም ሲሉ አሳስበዋል።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version