አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በፈረንጆቹ 2024 የወርቅ ዋጋ ከፍ እና ዝቅ በማለት መዋዠቅ ሲያሳይ የቆየ ሲሆን በዓመቱ ከፍተኛው ዋጋ 2 ሺህ 607 ዶላር ነበር፡፡
ይሁን እንጂ በፈረንጆቹ 2025 ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
በዛሬው ዕለት በእስያ ገበያ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ ከ4 ሺህ ዶላር በማስመዝገብ በታሪክ ከፍተኛው ሊሆን ችሏል።
ይህም ከፈረንጆቹ 1970 ወዲህ በዓለም ገበያ ውስጥ የታየ ከፍተኛ የወርቅ ዋጋ ጭማሪ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
የአሜሪካ መንግስት እስከ ቀጣዩ በጀት አመት ድረስ መስሪያ ቤቶችን መዝጋቱ እንዲሁም በፈረንሳይ እና ጃፓን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ለወርቅ ዋጋ ማሻቀብ ምክንያት መሆናቸውን ሲኤንቢሲ ዘግቧል።
በሚኪያስ አየለ