አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ተወካይ ካጃ ካላስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በኅብረቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ስለማጠናከር እንዲሁም በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ መምከራቸውን ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ በቤልጂየም ብራሰልስ እየተካሄደ ከሚገኘው 2ኛው የግሎባል ጌትዌይ ፎረም ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡