አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ያከናወነቻቸው ተግባራት የሚደነቁ ናቸው አሉ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳሲልቫ፡፡
2ኛው የግሎባል አሊያንስ ኢኒሼቲቭ የሀገራት ትብብር መድረክ በጣልያን ሮም እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም የምግብ ፎረም ጎን ለጎን ተከናውኗል፡፡
በመድረኩ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳሲልቫ፣ በጣልያን ኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ እንዲሁም የሌሎች ሀገራት መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሉላ ዳሲልቫ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸው ተግባራት የሚደነቁ ናቸው፡፡
በተለይም በግብርናው ዘርፍ በምግብ ራስን ለመቻል የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ደሚቱ በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባከናወነቻቸው ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጪነት የተተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል ነው ያሉት፡፡
መርሐ ግብሩ የእንቁላል፣ ወተት፣ ማርና ዓሣ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ማድረጉን አምባሳደሯ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ግሎባል አሊያንስ ኢኒሼቲቭ የሀገራት ትብብር በብራዚል አነሳሽነት የተፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በፍሬሕይወት ሰፊው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!