አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ሐዘናቸውን በመግለጽ ነፍሳቸው በሰላም እንድታርፍ ተመኝተዋል።
ራይላ ኦዲንጋ ባደረባቸው የልብ ሕመም በሕንድ ሀገር ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።