አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አየር ኃይል የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ ለመፈፀም በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል አሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ፡፡
የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር ኦፕሬሽን በግዳጅ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ክፍሎች እውቅና ሰጥቷል፡፡
ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት÷ተቋሙ የሚሰጠውን ተልዕኮ እና ግዳጅ ለመፈፀም በከፍተኛ የዝግጁነት አቅም ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል ።
አየር ኃይል በአጭር ጊዜ ባከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች አስደናቂ ስኬቶችን አስመዝግቧል ያሉት ዋና አዛዡ ÷ ይህም የአመራሩና የአባላቱ የጋራ ሥራ ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
አየር ኃይል ም/አዛዥ ለአየር ኦፕሬሽን ብ/ጄ ተስፋዬ ለገሰ በበኩላቸው÷ ክፍሉ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በንቃት በመጠበቅ የተቋሙን የውጊያ ዝግጁነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ግዳጃቸውን በብቃት ለተወጡ ክፍሎች የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት መሰጠቱንም የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ሌ/ኮ ውብሸት ቸኮል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!