አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የግንባታ እጆች ተቋማት ናቸው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትርና የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይህንን ያሉት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት በጉምሩክ ኮሚሽን ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎችን በተመለከቱበት ወቅት ነው።
የተቋማት ትብብር የኢትዮጵያን ማንሠራራት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸው ÷ ተቋማት በመደመርና በትብብር የጋራ ዕድገትን ለማረጋገጥ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በተቋማዊ የለውጥ ሥራዎች ውስጥ የሚገኙ እንደ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ጉምሩክ ኮሚሽን ያሉ ሀገራዊ ተቋማት በጋራ መስራታቸው ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በተቋማዊ ሪፎርም ማለፉን አስታውሰው ÷ በዚህም አሰራሮቹን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ መቻሉን ተናግረዋል።
የኮሚሽኑ ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎች በተገልጋይ እርካታና በሀገራዊ እድገት ሚናውን እንዲያሻሽል አስችለውታልም ነው ያሉት።
በሰለሞን በየነ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!