Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የመረጃ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሁራን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በመረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ አተገባበር አቅምን ከማላቅ ባሻገር የመረጃ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ ነው አሉ።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህር ሀብታሙ ፋንታ (ዶ/ር) እና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህር ዳዊት አባተ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፥ ስትራቴጂው ኢትዮጵያን ለዲጂታል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን የሚያደርግ ነው።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቋማትን አቅም በማጠናከር ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ተደራሽነትን ከማሳደግ ባሻገር የመረጃ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ፣ አካታችና ኢኖቬቲቭ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል መሆኑንም ነው የገለጹት።
የመረጃ አሰባሰብና ትንተናን አቅም የሚያዘምንና ወረቀት ተኮር የሆኑ አገልግሎቶች መሉ ለሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ለመቀየር የሚያስችል እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ምሁራኑ ባለፉት ዓመታት ሲተገበር የቆየው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በዲጂታል ስርዓቱ ላይ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን ገልጸው፥ መንግስታዊ አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ለህዝብ የቀረበና የተቀላጠፈ እንዲሆን ማስቻሉንም አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ በዘርፉ ውጤታማ እንድትሆን በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተፈጠረው መነሳሳት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት፡፡
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የዲጂታል የህዝብ መሰረተ ልማት፣ ስማርት ከተሞች፣ ድንበር ተሻጋሪ ዲጂታል ንግድ፣ ዲጂታል ሉዓላዊነትን የመሳሰሉ ጽንሰ ሃስቦችን አካቶ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
በአስጨናቂ ጉዱ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version