Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ በራይላ ኦዲንጋ አስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር ላይ ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ አስከሬን የክብር ሽኝት መርሐ ግብር በናይሮቢ ብሔራዊ ስታዲየም ተካሂዷል።

በሽኝት መርሐ ግብሩ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የራይላ ኦዲንጋ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ፖለቲከኞች እና ኬንያውያን ተገኝተዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ በህይወት ዘመናቸው ለፍትህ፣ ዴሞክራሲና ሀገራዊ አንድነት ታግለዋል ብለዋል።

Exit mobile version