Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት የሕዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክረምቱ ወራት ማሕበረሰቡ ላይ የኑሮ ጫና ሊያሳድሩ የሚችሉ ተግባራትን በመለየት ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በዚህም የኑሮ ውድነት ጫናን ከመቀነስ አኳያ የገበያ ማረጋጋት፣ ምርት በብዛት እንዲገባ የማድረግ፣ ገበያ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ብልሽቶችን የመቆጣጠር እና የሕዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል ያስቻሉ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
የክረምት ወቅት ተጽዕኖ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖች ላይ ጫና እንዳያሳድር ከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወን ለሕዝቡ ያለውን ወገንተኝነት በተግባር ማረጋገጥ መቻሉን ጠቅሰዋል።
የሀገር ባለውለታዎችን፣ አቅመ ደካሞች እና ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመለየት በሰው ተኮር ሥራዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በዓላት እሴታቸውን ጠብቀው በድምቀት እንዲከበሩ ብሎም የሕዝብ አብሮነት እንዲጠናከርባቸው መደረጉን ነው ያስረዱት፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የኮንፈረንስ ቱሪዝም የስበት ማዕከል እንድትሆን በማድረግ በርካታ ሀገር እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሉን ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version