Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ፕሮጀክቶች የሥራ ፈጠራና የጎብኝዎችን ዕድል የሚያሰፉ ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ያሉ ፕሮጀክቶች የሥራ ፈጠራ ዕድልን እና የጎብኝዎችን ዕድል የሚያሰፉ ናቸው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በባሌ ዞን በነበረን የሁለተኛ ቀን ቆይታ የወልመል ወንዝ የመስኖ ልማት እና ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ጉብኝት ባሻገር ወደ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሀረና ክላስተር በመገኘት ምልከታ አድርገናል ብለዋል።

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በሃረና ደን የሪራ ኢኮ ሎጅ እና ከባቢውን ብሎም የመመገብያ ስፍራዎችን፣ በእግር እና መኪና መንገዶች የቡና ሱቆችን፣ የምግብ አዳራሾችን እስከ ቱሉ ዲምቱ የከፍታ መወጣጫ ስፍራዎች የሚያካትቱ እንደሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ዘላቂ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች የአካባቢ የሥራ ፈጠራ ዕድልን እና የጎብኝዎችን ዕድል የሚያሰፉ በመሆኑ በልዩ ምልከታ የሚታዩ ናቸው ብለዋል።

Exit mobile version