አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል፡፡
በሥርዓተ ቀብሩ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ኡለማዎች፣ ደረሳዎች፣ ኡስታዞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡
ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ረፋድ ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው ፒያሳ ወደ ሚገኘው (በኒ) መስጂድ ሽኝት ተደርጎ ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ የዱዓ (ፀሎት) እና ሰላት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
በተጨማሪም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒዬም አዳራሽ የዱዓ እና ሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከ50 ዓመታት በላይ በዘለቀ የአዲስ አበባ ቆይታ ቅዱስ ቁርዓንን ከ300 ጊዜ በላይ በትርጉም አስተምረዋል።
በ1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሲመሰረት የምክር ቤቱ አባልና የዑለማ ሊቀመንበር ነበሩ፡፡
ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡
በጌታሰው የሽዋስ