Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሉሲዎቹ በታንዛኒያ አቻቸው ተሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻቸው 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ሉሲዎቹ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የመጨረሻውን የማጣሪያ ጨዋታ 11 ሰዓት ላይ በታንዛኒያ አዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ነው ከታንዛኒያ አቻቸው ጋር የተጫወቱት።
በጨዋታው የተሸነፉት ሉሲዎቹ÷ የመልስ ጨዋታውን ከሰባት ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ያደርጋሉ፡፡
ኢትዮጵያ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችው በ2012ቱ የኢኳቶሪያል ጊኒ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Exit mobile version