Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ እውቀት እንዲገበዩ…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች የዘመኑን ዲጂታል አሰራር  እና ቴክኖሎጂ የሚመጥን ትምህርት እንዲቀስሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው አሉ የኮሌጁ ዲን አቶ ተሰፋዬ አድማሱ ፡፡

የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ  እና ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን የቴክኖሎጂ እውቀት ለማሳደግ በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

አቶ ተሰፋዬ አድማሱ በዚህ ወቅት ÷ ለተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች ክህሎት መር የሆነ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በተለይም ዘመኑ የደረሰበትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ በትክክል በመረዳት ሥራ ፈጣሪ ወጣት ለማፍራት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ የተማሪዎችን የቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጠራና ተነሳሽነጽ እንዲሁም የዲጂታል እውቅት ለማበረታታት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከአዳዲስ የኢንዱስትሪ አዝማሚያዎች ጋር እንዲያስተሳስሩና እና የቴክኖሎጂ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እንደሚያግዝም ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ የመምህራን አቅም ለማጎልበት የቴክኖሎጂ ስልጠና መስጠት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ የፕላትፎርም ዳይሬክተር ጉኦ ዝሆንግሌይ በበኩላቸው÷ተማሪዎች በዲጂታል እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዘመኑን የዋጀ እውቀት እንዲቀስሙ በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version