አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ የናይጄሪያውን የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ዎሌ ሾይንካ ቪዛ መሰረዟ ተሰምቷል።
የ91 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ደራሲ ዎሌ ሾይንካ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሲሆኑ÷ ከአሜሪካ የተሰጣቸው ስደተኛ ያልሆኑ ቪዛ መሰረዙን እና እንደገና አሜሪካን ለመጎብኘት ከፈለጉ በድጋሚ እንዲያመለክቱ መነገራቸውን ገልጸዋል።
በናይጄሪያ ሌጎስ የሚገኘው የአሜሪካ ቆንጽላ የቪዛውን መሰረዝ ለማጠናቀቅ ፓስፖርታቸውን ይዘው እንዲቀርቡ መልዕክት እንደላከላቸውም ተናግረዋል።
አሁን ላይ ቪዛ የለኝም፤ ከዩናይትድ ስቴትስ በግልጽ ታግጃለሁ ያሉት ደራሲው÷ እኔን ማየት ከፈለጉ የት እንደሚያገኙኝ ያውቃሉ ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2016 ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ ዙር ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን በመቃወም የመኖሪያ ፈቃዳቸውን እንደቀደዱም ጠቁመዋል።
የኖቤል አሸናፊው ቪዛ መሰረዝን በተመለከተ በናይጄሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እስካሁን ምንም አስተያየት አለመስጠቱን ዘ ቴሌግራፍ ኦንላይን ዘገባ አመላክቷል።
በፈረንጆቹ 1986 በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ዎሌ ሾይንካ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በአስተማሪነት ሲሰሩ እንደነበር ተመላክቷል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

