አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የድሬዳዋ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ግንባታ ለማከናወን ስምምነት አድርጓል፡፡
ሚኒስቴሩ ስምምነት ያደረገው ከዮት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር ነው፡፡
በዚሁ ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ የድሬዳዋን ህዝብ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ዮት ኮንስትራክሽን በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ስራውን አጠናቅቆ እንዲያስረክብ አሳስበዋል፡፡
ፕሮጀክቱ መንግስት ከተሞችን ንፁህና ለእይታ ማራኪ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጋር የተቆራኘ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በአካባቢው ለሚገኙ ሴቶችና ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም አስረድተዋል፡፡
የዮት ኮንስትራክሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሃንስ ሙሉጌታ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለሀገር ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባት በጥራትና በወቅቱ ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
ግንባታና ጥገናው ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የሚከናወን ሲሆን በውሉ መሰረት በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ጌትነት ስሜ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

