አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የግብርና እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
የፓርቲው አመራሮች ባለፉት 10 ቀናት በአዳማ ከተማ ስልጠና ሲወስዱ ቆይተዋል።
ሰልጣኞቹ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ በኩታገጠም እየለማ ያለውን የፓፓያ እና የሙዝ ማሳ ተመልክተዋል፡፡
በኩታገጠም እየለማ ያለውና ሬድ ረዲ የሚባለው የፓፓያ ዝርያ ከአንድ ዛፍ ላይ እስከ አንድ ኩንታል ምርት ሊያስገኝ እንደሚችል በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
አመራሮቹ በዞኑ ሉሜ ወረዳ እየተካሄደ የሚገኘውንና ለ80 ወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠረው የዓሣ ኃብት ልማት ጎብኝተዋል።
የዓሣ ኃብት ልማት ሥራውን ጨምሮ በፓርቲው አመራሮች የተጎበኙት የልማት ሥራዎች ሌሎች ክልሎች ጥሩ ተሞክሮ ያዩበት መሆኑ ተገልጿል።

