Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋሲል ቅርስነቱን ጠብቆ ደረጃውን የጠበቀ የቱሪስት መዳረሻ መሆን የጎንደርን ትንሳዔ የሚያሳይ ነው – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋሲል አብያተ መንግሥታት ግንብ ቅርስነቱን ጠብቆ ለጎብኚዎች በሚመች ሁኔታ ደረጃውን የጠበቀ የቱሪስት መዳረሻ መሆን የጎንደርን ትንሳዔ የሚያሳይ ነው አሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር።

አፈ ጉባኤ አገኘሁ በጎንደር የልማት ስራዎች ጉብኝት ዙሪያ በሰጡት አስተያየት÷ ጎንደር በሀገሪቱ ከሚገኙ ጥንታዊ፣ ታሪካዊና ትልቅ ከተማ እንደሆነ አንስተው÷ ካለፉት መንግሥታት የሚገባውን ትኩረት አለማግኘቱን ተናግረዋል።

የፋሲል ቤተመንግሥትን እንደ አንድ የቱሪስት መዳረሻ ከማየት ባለፈ ተገቢ የሆነ ጥበቃ እና እንክብካቤ እየተደረገለት እንዳልነበር አስታውሰው÷ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትኩረት አድርገው ከሰሯቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ እምቅ ሃብቶች ገልጦ የማሳየት ስራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የፋሲል አብያተ መንግሥታት ግንብ ዓይናችን እያየ ሊፈርስ ነበር በማለት ገልጸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከነበረበት የተሻለ ሆኖና በሚገባ ተጠግኖ ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

ቅርስነቱን ጠብቆ ለጎብኚዎች በሚመች ሁኔታ ደረጃውን የጠበቀ የቱሪስት መዳረሻ መሆን የጎንደርን ትንሳዔ የሚያሳይ እንደሆነም አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የመገጭ ግድብ ፕሮጀክት ካለፈው አንድ ዓመት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የተሻለ ደረጃ ላይ ደርሶ ውሃ መያዝ መጀመሩን ጠቁመዋል።

ይህም ለጎንደር እና ለአካባቢው ልማት ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ገልጸው÷ ወደ 30 ሺህ ሄክታር መሬትን ለማልማት እና በጎንደር ዙሪያ ያለውን አቅም ለመጠቀም እንደሚያስችል አስረድተዋል።

እንዲሁም የጎንደር ከተማን መሰረታዊ የመጠጥ ውሃ ችግርን የሚቀርፍ እና የከተማዋን መልክ ለመቀየር ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራበት ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችም ተፋ ሰጪ መሆናቸውን በማንሳት በከተማዋ ተፈጥሮን በጠበቀ መልኩ የተሰራው ስራ ቀላል የሚባል እንዳልሆነም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የገበታ ለሀገር ኢኒሼቲቭ የጎርጎራ ኢኮሊጂ ለአካባቢው ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ ከመሆን ባሻገር በጎርጎራ ላይ ትልቅ የኮንፈረንስ ስራ መስራት የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version