Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

 

ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡

የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተመላክቷል፡፡

የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የአስክሬን ሽኝትና ቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ማክሰኛ ሕዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከናወንም ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version