ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተመላክቷል፡፡
የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የአስክሬን ሽኝትና ቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ማክሰኛ ሕዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከናወንም ተጠቁሟል፡፡