አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰላምን በማጽናት ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን መረጋገጥ ቁልፍ የሆነው ታሪካዊና ሕጋዊ የወደብ ባለቤትነታችንን ማረጋገጥ ቀጣዩ ጉዟችን ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ።
5ኛው ሀገር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የሰላም ጉባኤ ‘ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለአብሮነት’ በሚል መሪ ሀሳብ በአርባ ምንጭ ከተማ በህዝባዊ ተሳትፎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ አቶ ጥላሁን ከበደ እንዳሉት፤ ሰላም ሲኖር ሰው እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ማህበረሰብ በሰብአዊ ልዕልናው ልክ ሰርቶ ለሀገር ዋልታና ማገር መሆን ይችላል።
ሰላም የሚረጋገጠው የራስን ሰላም አስጠብቆ ሌላውም በሰላም እንዲኖር ማድረግ ሲቻል እንደሆነ ገልጸው፤ ሃይማኖቶች ለሰላም መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የለውጡ መንግስት ባሳየው ጠንካራ ስራ ባለፉት ዓመታት በተለይም በልማት በኩል ስንዴ ከውጭ ከማስገባት ወደ ውጭ መላክ መቻሉን ገልጸው፤ ለልማት እና ለሰላም ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መንግስት የጀመራቸውን የጂኦስትራቴጂ እቅዶችን ለማሳካት ሰላም ዋናው መሳሪያ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰላምን አጥብቀው መሻት አለባቸው ብለዋል።
በተያየ ጊዜ ከሰላማዊ መንገድ ወጥተው የነበሩት ኃይሎች ወደ ሰላም ተመልሰው በልማት ስራ ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ቀጣይ የተያዙ ትልሞች እንዲሳኩ ሰላምን ለማጽናት እንደሚሰራ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዓለምን ባስደመመ እርጥብ ሳርን በመያዝ ፀብን በማብረድ እርቅ ያወረዱ የጋሞ አባቶች አረዓያነት ለዘላቂ ሰላም ትልቅ ማሳያ ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ናቸው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሀይማኖታዊ አስተምህሮ ያፈነገጡ፣ ሰላምን በማደፍረስ አላስፈላጊ ዋጋ የሚያስከፍሉና የልማት አቅማችንን የሚሸረሽሩ ድርጊቶች ይስተዋላሉ ብለዋል።
ይህንን አደገኛ ልምምድ ለማረም በጋራ ትውልዱን ማስተማር እና ማነጽ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በመለሰ ታደለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

