አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ናቸው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)።
በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ ማሳያ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ በተለይም በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ናቸው ብለዋል።
በፖለቲካው መስክ የነበረውን አግላይነት በማስቀረት ሁሉንም አሳታፊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል።
ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በኋላ በመንግሥት ምስረታ ሂደት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በካቢኔ ውስጥ በማሳተፍ በጋራ እንዲሰሩ መደረጉ አስታውሰው፤ የተለያዩ አመለካከቶች የያዙ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራዊ ጉዳዮች በጋራ መስራት ችለዋል ብለዋል፡፡
ይህ ሂደት መግባባት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲ ለመገንባት ጅማሮ እንደሆነም ተናግረዋል።
ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በፖለቲካው ዘርፍ እየተገኙ ከሚገኙ ስኬቶች መካከል አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ አቅጣጫ ተቀምጦ ትጥቅ ያነገቡ ቡድኖች ሰላማዊ ፖለቲካ እንዲያራምዱ በሩ ክፍት መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ሀገራዊ የፖለቲካ ባህል መቀየሩን ያሳያል ብለዋል፡፡
ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የመንግሥት ጥረት ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌና በሌሎችም ክልሎች የነበሩ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ በመፍታት በክልሎቹ ሰላማዊ የልማት እንቅስቃሴ መካሄድ መጀመሩን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ከታጠቁ አካላት ጋር በመነጋገር ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ተደርጓል ነው ያሉት።
አሁን ላይ በክልሎቹ የሰላም በር ተከፍቶ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

