Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መንግሥት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መንግሥት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሰራ ነው አሉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በደሴ ከተማ የተመለከትናቸው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት ማዕከል እንዲሁም የእንጀራ መጋገሪያ አዳራሽ ስራዎች የሕዝባችንን የየዕለት ችግሮች ለመፍታት ለምናደርገው ጥረት ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

የግብይት ማዕከሉ ዋና ዓላማ አምራቾች እና ሸማቾችን በማገናኘትና በመካከል ያለውን የተንዛዛ የግብይት ሰንሰለት በማሳጠር ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እና የእንስሳት ተዋጽኦዎች ግብይት ይካሄድባቸዋልም ነው ያሉት።

የደሴ ከተማ የቧንቧ ውሃ የእንጀራ መጋገሪያ አዳራሽ ግንባታ እንጀራ በመጋገር ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ምርታማነትን በማስፋፋት የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የብልጽግና ጉዟችን ሁሉንም ማሕበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ማሕበራዊ ፍትህን ያረጋገጠ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ራዕይ የሚመራ ነው ሲሉም አመላክተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version