አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ማሌዥያ ትብብራቸው ለረጅም ዓመታት የዘለቀ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የሀገራቱን አጋርነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል በጋራ መርሆዎች ላይ የተመሠረተና እያደገ የመጣው ጥልቅ አጋርነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ተናግረዋል።
ሀገራቱ ትብብራቸው ለረጅም ዓመታት የዘለቀ እንደሆነ በማንሳት÷ ግንኙነቱ በበርካታ ዘርፎች ትብብርን ለማሳደግ አዳዲስ በሮችን የከፈተ ነው ብለዋል።
መሪዎቹ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ በዚህም የወደፊት ትብብርን ብሩህ እና ጠንካራ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር በበኩላቸው ጉብኝታቸው ከዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ይልቅ ቤተሰባዊ መሆኑን ገልጸው÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማስፋት ያላቸውን ፍላጎት አመላክተዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ውጤታማ ትብብር ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ በደቡብ – ደቡብ ትብብር ውስጥ ያላትን ተሳትፎና እንደ ብሪክስ ላሉ ዓለም አቀፍ መድረኮች የምታደርገውን ድጋፍ አድንቀው÷ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ተደማጭነት እያደገ መምጣቱንም ጠቅሰዋል።
የሀገራቱ የወደፊት ትብብር በኢንቨስትመንት፣ ንግድ፣ ትምህርት፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ባህልና ክልላዊ የገበያ ውሕደት ላይ እንደሚያተኩርና ይህም የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ማህበር (ASEAN) እና በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚ መካከል ትስስር የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

