Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመስራት …

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና አዘርባጃን ሪፐብሊክ በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።

በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራው ልዑክ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ በዛሬው ዕለት ከመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሯ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ መሠረተ ልማቷን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች።

በወታደራዊ ቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ አቅም እና ተያያዥ ጉዳዮች ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ልምድ ለመቅሰም ዝግጁ መሆኗን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ፍላጎት ያላት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቩጋር ሙስታፋይ በበኩላቸው፥ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር በተለይም በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ልምዷን ለማከፈል ዝግጁ እንደሆነች አረጋግጠዋለ።

ሀገራቸው ኢትዮጵያን የመከላከያ ኢንዱስትሪ አጋሯ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ የአዘርባጃንን ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version