Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መዲናዋን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጉ ሆስፒታሎች ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመገንባት ላይ የሚገኙት ሆስፒታሎች አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ ናቸው አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባ አዳነች ለሕዝቡ ጥያቄ ተጨባጭ ምላሽ እየሰጡ ከሚገኙ ሥራዎች መካከል አንዱ የሆነውን የሦስት አዳዲስ ሆስፒታሎች አጠቃላይ የግንባታ ሒደት ገምግመዋል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ሆስፒታሎቹ ከዚህ በፊት ከነበሩት የተሻለና የላቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ሆነው እየተገነቡ ሲሆን÷ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተሞች እየተገነቡ የሚገኙት ሆስፒታሎቹ ከዚህ ቀደም ሆስፒታል ባልነበረባቸው አካባቢዎች መገንባታቸው የሕክምና ፍትሃዊ ተደራሽነት ማስፋት ያስችላሉ ብለዋል፡፡

ሆስፒታሎቹ 1 ሺህ 500 አልጋ እንደሚኖራቸው እና ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎችን ማስገባት ቀጣዩ ትኩረታችን ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች÷ ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት እንደሚሰጡ አመልክተዋል፡፡

ለሕዝቡ ጥያቄ ተጨባጭ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር በሚሰጡት ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት የልሕቀት ማዕከል ሆነው እንደሚያገለግሉ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከአዲሶቹ ሆስፒታሎች ግንባታ በተጨማሪ በሚኒሊክ፣ ራስ ደስታ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች አዲስ ሆስፒታል የመገንባት ያህል የማስፋፊያ ሥራ መከናወኑን ነው ያብራሩት፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ ሥራ ተጠናቅቆ በቅርቡ ሥራ መጀመሩን ከንቲባዋ አስታውሰዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version