Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ከሚገኘው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

በዚህም በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች እና በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በትኩረት መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

እንዲሁም ትብብርን በማጠናከር ዘላቂ እና አካታች ዕድገትን ለመደገፍ ባሉ ዕድሎች ላይ መወያየታቸውን አመልክተዋል፡፡

ለአይኤምኤፍ ዘላቂ ትብብር ምስጋና ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ÷ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተቋሙ ጋር የተለዩ የጋራ ትኩረቶችን ለመፈፀም ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

Exit mobile version