Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባዔ ጎን ከአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሃሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ከቡድን 20 ጉባዔ ጎን የአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሃሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር የመወያየት እድል አግኝተናል ብለዋል።

ውይይታቸውም ስትራቴጂካዊ ትብብርን በማጠናከር ለበለጠ የጋራ ርምጃ እድሎችን መመልከት ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።

Exit mobile version