አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 21 ሺህ 326 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 336 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ 58 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።
ከዚህ ባለፈ የ28 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 600 መድረሱንም አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 370 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 308 መድረሱም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ እስካሁን 672 ሺህ 637 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው እና የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኝ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 148 ሲሆን፥ ከእነዚህም 255 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

